የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራር እና ሰራተኞች 18ኛውን ሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነት፣

ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል አከበሩ ፡የሰንደቅ ዓላማውን አከባበር አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ባስተላለፉት መልዕክት ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ የህዝቦቿን አንድነት እና የብሔራዊ ማንነቷን የሚገልጽ፣ አባቶቻችን ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉበት የታላቅነትና የኩራታችን ምንጭ ነው፤ እኛም በምንሰጠው ስልጠና የሀገርን ፍቅርና ክብር ለሰልጣኞቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን ለናሸጋግረውና ልንጠብቀው ይገባል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙር ሰንደቅ ዓላማውን በመሰቀል አክብረዋል ፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et