በራሱ የሚተማመን በክህሎት የዳበረ ብቁ ዜጋ ለማፍራት የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑ ተገለጸ።

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሥራና ክህሎት ሚ/ር፣ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመጡ ኃላፊዎች የ2018 እቅድ እና የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማጠናከር መንግስት ከአምስቱ ቁልፍ ዘርፎች አንዱ ቱሪዝም ን በማድረጉ ይህን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሁሉም በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ስልጠና የሚሰጡ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆችና ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት አብሮ በመስራት፣ የተሰሩትን በመገምገም በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በዚህ የትብብር ሥራ በራሱ የሚተማመን በክህሎት የዳበረ ብቁ ዜጋ ለማፍራት የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት አስተዋጽኦ ጉልህ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የተቋሙ 2017 በጀት ዓመት ሪፓርትና የአስር ዓመት ፍኖተ ካርታ 2018 በጀት ዓመት እቅድ በአቶ ዳግም አዲሱ እና በዶ/ር አስቻለው አደራ ቀርቧል።
በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ከተሳታፊዎቹ እንደተገለጸው ተቋሙ እንደሀገር በዘርፉ አንጋፋ ከመሆኑ አንፃር በስልጠና ዘርፍ ኢንደስትሪው የሚፈልገውን የሰው ሃይል ከማቅረብ አንፃር በስፋት መስራት እንደሚጠበቅበት እቅዱም ከፍ ባለደረጃ መስፋት እንዳለበት ገልጸዋል።
ተቋሙ በቱሪዝም ዘርፍ መንግስት ከሰጠው ትኩረት አንፃር ከክልሎች ጋር ያሉ ጅምር ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይጠበቅበታልም ተብሏል።
ተሳታፊዎቹ ከገበያ ፍላጎት አንፃር ከመደበኛ ስልጠናው ባሻገር አጫጭር ስልጠና ላይ የሚሰጠው ስልጠና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት መታቀዱ እንደ ጥሩ ጅምር ወስደው ከቁጥር አንፃር ሰፋ ቢል የሚል ሃሳብ ተሰጥተዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከክልሎች ጋር በጥናትና ምርምር ዘርፍ ባህላዊ ምግቦች ላይ እየሠራ ላለው ሥራ እውቅና ስጥተዋል።
ከተሳታፊዎች የቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል።
የ10 ዓመቱ ፍኖተ ካርታ በየደረጃው ባሉ የዘርፉ ባለድርሻዎች ተገምግሞ በሚሰጠው ግብዓት ዳብሮ ሥራ ላይ ይውላል ተብሏል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et