ሠራተኛው ዘመኑ በሚፈልገው ልክ ቴክኖሎጂን መላመድ እንደሚገባው ተጠቆመ።የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሠራተኞች እና አሰልጣኞች ዘመኑ በሚፈልገው ልክ ከቴክኖሎጂ ጋር መላመድ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በፕሮግራሙ የተገኙት የተቋሙ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደገለጹት ዘመኑን የሚመጥን ተቋም ለማድረግ የሠራተኛው የአስተሳሰብ እና አተያይ ሁኔታ ዘመኑን የሚዋጅ መሆን እንደለበት ተናግረዋል። ዘመኑ ምንም ያክል ቢዘምን ያለሰው አይሆንም ስለዚህ ራሳችንን ከቴክኖሎጂ ጋር ማዋሃድ እንዳለብን ጠቁመዋል።
ለሠራተኛው ይህን ስልጠና ዶ/ር ደመቀ አፈወርቅ የሰጡ ሲሆን በገለፃቸውም ሁለት አይነት አስተሳሰቦች እንደሉ እነሱም Linear Thinking and System thinking ለተቋም አስፍቶ ማሰብ ጠቃሚ ነው ብለዋል።
ሰዎች በሥራ ቦታቸው ለሚገጥሟቸው ችግሮች ራሳቸውን ተጠያቂ ካደረጉ ቀጣይ ያ ስህተት እንደማይደገም ፤ መልካም ነገር በመስራት ምስጉን ሠራተኛ መሆን እንደሚቻል “ጽድቅ ና ኩኔኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም” በሚል አስተሳሰብ መልካም ማድረግ ለተቋምም ለራስም የሚያሳርፍ መሆኑን አንስተዋል።
ሠራተኛው በተነሱ ሀሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ሁሉም በተቋም ቆይታው በመልካም ተግባር መታወቅ እና በቴክኖሎጂ ለመዘመን ቃል ገብቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments