ግንቦት 12/2014 የምርምር ጉባኤው በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት፣ በሰመራ ዩኒቨርሲቲና በአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ በጋራ የተዘጋጀ ነው።
ጉባኤው “ቱሪዝም ለሥራ እድል ፈጠራ ያለው ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ መሆኑን የገለፁት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዳሬይክተር አስቴር ዳዊት የኢኮ-ቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎች፣ የአስጎብኚ ማኅበራት፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች ይሳተፋሉ ብለዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መሀመድ ኡስማን (ዶ/ር) በበኩላቸው የአፋር በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች የሚገኙበት ክልል ነው ያሉ ሲሆን ይህንን እምቅ ኢኮኖሚያዊ ሃብት ለመጠቀም ጉባኤው በጎ አስተዋፅኦ አለው በማለት ገልፀዋል።
ከሰላምና ፀጥታ ጋር በተገናኘ በክልሉ የቱሪስት ፍሰት የተቀዛቀዘ ሲሆን ጉባኤው ዘርፉን ከማነቃቃት አኳያ የራሱን ሚና ይጫወታል ያሉት ደግሞ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አህመድ አብዱር ቃድር ናቸው።