በዚህ ለሁሉም ሰው ክፍት በሆነው ፕሮግራም ላይ ከ200 በላይ ሆቴሎችና በዘርፉ የተሰማሩ በርካታ አገልግሎት ሰጪዎችና አቅራቢዎች ይሳተፉበታል፤ ሰራተኞችን ይመላምላሉ፤ ሲቪዎችን ይቀበላሉ፤ ራሳቸውን ያስተዋውቁበታል፤ ትስስርም ይፈጥሩበታል።

እርሶም ሰኞ ሕዳር 29, ከቀኑ 8:30 እስከ ምሽቱ 12:00 እንዲሁም ማክሰኞ ሕዳር 30 ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 9:30 በሚካሄደ በዚህ ዝግጅት ላይ ተገኝተው ትስስር ይፍጠሩ፤ ያመልክቱ፤ ባለ ስራ ለመሆን አጋጣሚውን ይጠቀሙ። ጎን ለጎንም በሚካሄዱት የቃለመጠይቅ ፤ የሲቪ አፃፃፍና መሰል ነፃ ስልጠናዎች ላይ በመገኘት ክህሎቶን ያዳብሩ ፤ ሲቪዎን በዘርፉ ባለሙያዎች ያስገምግሙ፤ እንዲሁም በሴክተሩ የተለያዩ አንገብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ የፓናል ውይይቶች ላይ በመሳተፍ ሃሳቦን ያጋሩ::

አዘጋጅ የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ከኦንፖይንት ማኔጅመነት ሶሉሽንስ ጋር በመተባበር።

አጋር ድርጅቶች የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፤ UNDP, GIZ፤ ኮካ ኮላ፤ ዘመን ባንክ ፤ ሃይኒከን ፤ዛይ ራይድ

ለበለጠ መረጃ www.jobfairethiopia.com እንዲሁም በፌስቡክ ገፃችን ያግኙን::

መግቢያ በነፃ!!