የቱሪዝምና የእንግዳ ተቀባይነት ሣምንት መክፈቻ

ለ8ኛ ጊዜ ከግንቦት 15/2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለሶስት ቀናት “ቱሪዝም ለሰላም፤ ሰላም ለቱሪዝም!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ሳምንቱን የሚያከብረው “ሰላም ለቱሪዝም፤ ቱሪዝም ለሰላም” በማለት የተለያዩ ትእይንቶችን ውድድሮችን እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በመዘርጋት መሆኑ ተገልጿል።

Read More

ጥናትና ምርምር

“ቱሪዝም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ” በሚል መሪ ቃል የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው። ==================== (ሚያዝያ 28/2013 ዓም) የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር “ቱሪዝም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው። በፕሮግራሙ መክፈቻ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ እና የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ቦርድ ሰብሳቢ የቱሪዝም…

Read More

የሚዲያ ሽፋንን እንድትሰጡን ስለመጠየቅ

ሀገር አቀፍ የቱሪዝምና ዕንግዳ ተቀባይነት ሳምንት (National Annual Tourism and Hospitality week) ለ8ኛ ጊዜ ከግንቦት 15 እስከ 17/2013 ዓ.ም. “ቱሪዝም ለሰላም፤ ሰላም ለቱሪዝም!” በሚል መሪ ቃል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለድርሻ አካላት እና የተቋሙ ማህበረሰብ በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለማክበር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ይህን ሃገራዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት የፕሮግራም…

Read More

የስራ ዕድል ማስታወቂያ

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል እያዘጋጀ ከሚገኘው 8ኛው የቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት ፕሮግራሞች መካከል አንዱ የሆነው የሰልጣኞች የስራ እድል ፈጠራ (job fair) ላይ በሆቴልና በቱሪዝም መስኮች የተሰማሩ ድርጅቶች ከተቋማችን ሰልጣኞች ቅጥር ለመፈጸም ዝግጅት ስላደረጉ ትምህርታችሁን የጨረሳችሁ ሰልጣኞች በሙሉ ኢቨንት ቢሮ ሲቪያችሁን እስከ ግንቦት 13/2013 ዓ.ም በማስገባት ዝግጅት እንድታርጉ እናሳውቃለን፡፡ የስራ ቅጥር የሚከናወንበት ቀን ግንቦት 16/2013…

Read More

ማስታወቂያ

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል በ2013 አዲስ በቀን መርሃ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህ ማስታወቂያ የሚመለከተው በ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የTVET መግቢያ ውጤት ያመጡትን ይሆናል። የምዝገባ መስፈርቱ የሚከተለው ሲሆን የ8ኛ ክፍል ካርድ እና የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ዋናውንና ኮፒውን በመያዝ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን!

Read More

8ተኛውን የቱሪዝምና እንግዳ ተቀባይነት ሳምንት

“ቱሪዝም ለሠላም፤ ሠላም ለቱሪዝም!” በሚል መሪቃል ከግንቦት 15-17/2013 ዓ.ም ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ሰላምና ቱሪዝም የማይለያዩ ጉዳዮች ናቸው፣ ቱሪዝም ሰላምን ለማስፈን ከፍተኛ ሚና እንዳለው ሁሉ የሰላም መኖር ለቱሪዝም እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

Read More