ማስታወቂያ

ለ2015 የትምህርት ዘመን ለመማር የተመዘገባችሁ አዳዲስ ሰልጣኞች በሙሉ የመግቢያ ፈተና ሰኞ መጋቢት 25/2015ዓ.ም የሚሰጥ ስለሆነ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን ረቡዕ እና ሀሙስ ፤ ምዝገባ የሚካሄድ ይሆናል። ሚያዚያ 2/2015ዓ.ም ሥልጠና ይጀምራል።ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከ1961ዓ.ም ጀምሮ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪ ግንባር ቀደም ተቋም ነው። ኢንስቲትዩቱ በሚሰጠው ሥልጠና ተፈላጊ የሆኑ ባለመያዎችን ከማፍራቱ ባሻገር በየወሩ የኪስ ገንዘብ መክፈሉ ልዩ ያደርገዋል።

Read More

የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላት የአመራርና አስተዳደር ስልጠና ወሰዱ።

መጋቢት 15/2015 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪየሺን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት በአመራርና አስተዳደር ዙሪያ ለኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላት ስልጠና ሰጥቷል።

Read More

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ

መጋቢት 7/2015ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአገራችን ለ47ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ “Digit ALL: Innovation and technology for gender equality.” ”ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ለጾታ እኩልነት” በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ደግሞ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

Read More

ቱ.ማ.ኢ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሚሄዱ ሰራተኞች ሥልጠና መስጠት ጀመረ

መጋቢት 5/2015ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ወደ ሳውዲ አረቢያ ለቤት ውስጥ ሥራ ለሚሄዱ ሰራተኞች ሥልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ ስልጠናውን አስመልክቶ የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ከኢፌዲሪ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት የቤት ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ ለመውሰድ ካለው ፍላጎት የተነሳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Read More