ማስታወቂያ

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ነባር ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ! የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ባወጣው መርሐ ግብር መሰረት ጥቅምት 07/2016 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እየገለጽን ለስልጠና ስትመጡ የተሟላ የደምብ ልብስና ለኢንዱስትሪው የሚመጥን (ጫማ፣የጸጉር አቆራረጥና ንጽህና) ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በትምህርት ገበታችሁ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንክ በመጠቀም የፌስቡክ ገጻችን ይጎብኙ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ

Read More

የደረጃ ሶስትና አራት ማስተማሪያ ሞጁሎች ዝግጅት ተጠናቀቀ፡፡

መስከረም15/2016 ዓ ም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሥራና ክህሎት ሚኒስተር ጋር በመተባበር ላለፉት አስራ አምስት ቀናት ሲዘጋጅ የቆየው የቱሪዝምና የሆቴል ዘርፍ የደረጃ ሶስትና አራት ማስተማሪያ ሞጁሎች ዝግጅት ተጠናቀቀ፡፡

Read More