ኢንስቲትዩቱ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የሰው ኃይል ልማት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባው ተጠቆመ የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዘርፎች አፈፃፀም ግምገማን አጠናቆ የተጠሪ ተቋማትን አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል፡፡ በዚህም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ የጀመራቸው የሪፎርም ተግባራት ተስፋ ሰጪ ናቸው፡፡

Read More

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ብሔራዊ ቤተመንግስትን ጎበኙ ቱ.ማ.ኢ የካቲት 20/2017 ዓ.ም

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በቅርቡ ታድሶ ለጎብኝዎች ክፍት በሆነው ብሔራዊ ቤተመንግስት ጉብኝት አደረጉ።የብሔራዊ ቤተመንግስት በ1948 ዓ.ም የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮበልዩ ክብረበዓልን ምክንያት በማድረግ የተገነባ ነው።ቤተመንግሥቱ የኢትዮጵያን ውጭ ግንኙነት ፣ የታሪክ አሻራዎች ፣ የአስተዳደር ሥርዓት በአጠቃላይ ከፍተኛ የጎብኝዎች መዳረሻ ሊሆኑ የሚያስችሉ እምቅ ሀብት ይዟል ። ቤተ መንግስቱ ውስጥ ከአፍሪካ ህብረት ምስረታ ጋር የተያያዙ ብዙ…

Read More

በቱሪዝም ዘርፍ ያለው የሥራ ገበያ ፍለላጎት እና የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦትና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

ከቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ጋር በትብብር መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡በመድረኩ በቱሪዝም ዘርፍ ያለው የሥራ ገበያ ፍለላጎት እና የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆነው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት አማካይነት የተጠና ጥናት ቀርቦ በግኝቶቹና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ተወያይተናል፡፡

Read More

የዓለም የቱሪስት አስጎብኚዎች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ ቱ.ማ.ኢ የካቲት 14/2017 ዓ.ም

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚዎች ማህበር ጋር በመተባበር የዓለም የቱሪስት አስጎብኚዎች ቀን በሀገራችን ለአምስተኛ ጊዜ “ቱሪስት አስጎብኚ የሰላም አምባሳደር ናቸው” በሚል መሪ ቃል በገነት ሆቴል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።እለቱን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደገለጹት የቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ቀንን ስናከብር ከሰላም መነሳቱ ቁልፍ ሀሳብ መሆኑን ጠቅሰው…

Read More

በትብብር ስልጠና ላይ ያሉ ሰልጣኞች ድጋፍ እና ክትትል ተደረገላቸው። ቱ ማ ኢ የካቲት 14/2017 ዓ ም

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2ኛ እና 3ኛ ዓመት ለትብብር ስልጠና በሆቴሎችና ቱር ኦፕሪተሮች የላካቸውን ሰልጣኞች ድጋፍ እና ክትትል አደረገላቸው፡፡ ቮኬሽናል ጋይዳንስና ካውንስሊንግና ትብብር ስልጠና አስተባባሪ አቶ ታደሰ ሞላ ለትብብር ስልጠና በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልል ከተሞች ባሉ ሆቴሎችና ቱር ኦፕሬተሮች ከ300 በላይ ሰልጣኞች የትብብር ስልጠና ላይ እንዳሉ ገልጸው፤ ሰልጣኞቹ ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የዛሬው ፕሮግራም…

Read More

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ ቱ.ማ.ኢ የካቲት 12/2017 ዓ.ም

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የብልጽግና ሁለተኛ ጉባኤ ላይ በተለይ በቱሪዝም ዘርፉና የሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ፓርቲው ያወጣቸውን አስር የትኩረት መስኮች መሰረት በማድረግ ምክክር አድርገዋል።በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ መንግስት ገለልተኛና ውጤታማ ሲቪል ሰርቫንት እንዲኖር የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም…

Read More

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለአካል ጉዳተኛ ህጻናት የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ቱ.ማ.ኢ የካቲት 08/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተለያዩ ክፍለ ከተማ ለተወጣጡ አካል ጉዳተኛ ህጻናት ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከEASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የትምህርት ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል። ተቋሙ በአካባቢውና አጎራባች ክፍለ ከተሞችም የተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ ተግባራትም እንደሚሳተፍ ይታወቃል። ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.e

Read More

ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የልህቀት ማዕከል ግንባታን አስመልክቶ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ

ቱ.ማ.ኢ የካቲት 08/2017 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በEASTRIP ፕሮጀክት አማካኝነት የልህቀት ማዕከል ለመገንባት እየተሰራ በሚገኘው ግንባታ ዙሪያ ከወረዳው ነዋሪ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደዋል ። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ አንድ ፕሮጀክት ሲገነባ ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚሰጠው ጠቀሜታ የስልጠና፣ የሥራ ዕድል እና ሌሎች የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን…

Read More

የጥናት ሰነዶች ርክክብ ተደረገ ቱ.ማ.ኢ የካቲት 05/2017 ዓ.ም

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ያጠናውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚረዱ አራት የጥናት ሰነዶችን አስረከበ፡፡ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የክልሉን ቱሪዝም ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚያስችሉ የቱሪስት ማፕ፣ የባህላዊ ምግብ ዝግጅት ጥናት፣ በአካባቢው የሚገኝ እምቅ የቱሪዝም ሀብት ጥናት እና የጉዞ ጥቅል ጥናትን የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ለክልሉ ባህልና…

Read More