በዓለም ባንክ ግዥ አሰራር ሥርዓት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ቱ.ማ.ኢ የካቲት 10/2016ዓ.ም
በዓለም ባንክ ግዥ አሰራር ሥርዓት ግንዛቤ ችግር የሚስተዋሉ የግዥ ሂደት መጓተትን ለማስቀረት ለኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላትና ግዥ አጽዳቂ ፣ ጥራት ኮሚቴ አባላትና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እያከናወነ የሚገኘውን የስልጠና ጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግሎት ለማሳካት በቴክኖሎጂ እየተሻሻለ የመጣውን የግዥ ሂደት ደምብና መመሪያዎችን በማወቅ ወቅቱን እና ጥራቱን የጠበቀ ግዥ ለመፈጸም ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ የሚታየውን በሆቴልና ቱሪዝም ሙያ የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት ለመቅረፍ አብሮ እየሰራ ከሚገኘው የዓለም ባንክ ‘EASTRIP’ ፕሮጀክት ግዥ በሚፈለግ ጥራትና ጊዜ ገደብ ውስጥ ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑንንም ጨምረው ገልጸዋል።
የዓለም ባንክ ግዥ አሰራር ስርዓትና መመሪያ ላይ የፕሮጀክቱ ፋይናንስ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሰማኸኝ ታምር ገለፃ አድርገዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et/