ኢንስቲትዩቱ ባለፉት ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ውይይት መድረክና የሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መርሐ ግብር ተጀመረ፡፡
ተ.ማ.ኢ ጥር 17/2017 ዓ.ም
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ውይይት እና የሰራተኞች የአቅም ግንባታ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሸ መንግስት የኢትዮጵያን ህልሞች ለማሳካት በተለይም በቱሪዝም ዘርፍ ሀገራችን የዓለም ቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው
ወደ ሀገራችን የሚመጡ ጎብኝዎችን በሚገባ ለማስተናገድ የሚመጥን ብቃት ያለው የሰው ማፍራት ከኛ ይጠበቃል ብለዋል። አቶ ጌታቸው ነጋሽ አክለውም ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን ብቃት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት ጥናት ላይ የተመሰረተ ዘርፎችን በመለየት ስልጠናዎች እየተሰጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በተለይ በላፉት ስድስት ወራት ውስጥ ኢንስቲትዩቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀራረብ ሰፊ ሥራዎች እንደተሰሩ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ እየተካሄደ የሚገኘው መድረክ የተሰሩ ስራዎችን ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ የተሻሉ ሥራዎችን ለመስራት በቀጣይ ጊዜ እቅዶች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ተቋሙ ከፍተኛ የሪፎርም ሥራ ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት የኢንስቲትዩቱ የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በሰነድ ዝግጅት፣በአበይት ሥራዎች ክንውን ፣ የሰው ሀይል ሙሌት፣ የቢሮ እድሳትና አጠቃላይ የተሰሩ ስራዎች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡

Recent Comments