ቱ.ማ.ኢግንቦት 19/2017 ዓ.ም በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት እና በጎንደር ዩንቨርስቲ ትብብር የተዘጋጀው የጥናትና ምርምር ጉባኤ የተለያዩ የቱሪዝም ዘርፉን ቀጣይነት የሚያመላክት እንዲሁም የዘርፉን እድገትና ተግዳሮት እንዲሁም ምክረ ሃሳብ የዳሰሱ የተለያዩ የጥናት ጽሑፎች ቀርበዋል።የምርምር ጉባኤውን ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደገለጹት የቱሪዝም ዘርፉ እድገት አዳዲስ የአሰራር ስርዓት መጠቀም ፣ፈጠራን ማበረታታት ፣የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማስፋት እና አዳዲስ ጥቅሎችን መጠቀም የሚል ቁልፍ ሃሳብ አንስተዋል።

ይህ የጥናትና ምርምር ጉባኤ የጎንደር ዩንቨርሲቲ 70ኛ ዓመት ክብረበዓል አካል ነው። በጉባኤው ስድስት የጥናት ጽሑፎች ቀርበዋል።
ተሳታፊዎችም በቀረቡ የጥናት ጽሑፎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et