ቱማኢ ግንቦት 25/2017 ዓ ምቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከተሰጡ ተልዕኮ አንዱ በዘርፉ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ማካሄድ ነው ።ስለሆነም በዘርፉ የተለያዩ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምር ሥራዎች ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ዛሬ በቱሪዝም ትምህርት ክፍል ቱሪጋይድ ሰልጣኞች ያሉበት ደረጃ ጥናት ‘Enhancing Tour Guiding skills of TTI REgular Trainees through Experiential learning and structured feebback mechanisms .’በሚል ርዕሰ በእጩ ዶ/ር አለምነህ ማርሻ እና በአቶ አብይ ንጉሤ የተካሄደ ጥናት ቀርቧል።
በዚህ ጥናት ላይ ተጨማሪ ግብዓት ለማሰባሰብ የሚያስችል ከአካዳሚክ ዘርፍ ለተወጣጡ ባለሙያዎች ጥናቱ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
ጥናቱን አስመልክቶ የተቋሙ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደገለጹት አጥኚዎቹ በራሳቸው ተነሳሽነት እንደዚህ አይነት ችግር ፈች ጥናትና ምርምር ማድረጋቸውን አመስግነው የግብዓት አሰባሰብ ሥራዎችም የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።
ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ ወደፊት ከሌሎች ጥናቶች ጋር በተቋም ደረጃ በሚታተሙ ጆርናሎች ይታካተታልም ተብሏል።
መሰል የጥናትና ምርምር ሥራዎች ውይይት በየአስራ አምስት ቀኑ የሚቀጥል እንደሆነም ተገልጿል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et


Recent Comments