ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች በዲግሪና በደረጃ ያሰለጠናቸውን 481 ሰልጣኞች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ለተመራቂዎች የስራ መመሪያ የሰጡት የሥራ ክህሎት ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል መንግስት ባለፉት ሰባት ዓመታት ለሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘርፉን ለማሳደግ በጥናትና ምርምር የተደገፉ በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እንዳከናወነ ገልጸዋል።
ተመራቂዎች የተሰጣቸው ሙያዊ ኃላፊነት ተምሮ ሰልጥኖ ስራ መያዝ ብቻ ሳይሆን፣ ሀገርን ማስተዋወቅ በመሆኑ ይህን ሀገራዊ ሀላፊነት በብቃት በመወጣት ለሀገራችሁ አምባሳደር እንድትሆኑ ሲሉ ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው በመዲናችን አዲስ አበባም ሆነ እንደሀገር የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች የተስፋፉበት ጊዜ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋማችን፣ ትኩረቱን በሆቴልና ቱሪዝም ሙያዎች ላይ አድርጎ የንድፈ ሃሳብ እና ተግባር ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል ብለዋል::
ተመራቂዎችም በሰለጠኑበት ሙያ እራሳቸውንም ሆነ ሀገራቸውን ለማገልገል ከውጭ ለሚመጡ ቱሪስቶችም በአግባቡ ሀገራቸውን ለማስተዋወቅ ቃል ገብተዋል፡፡