ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ያጠናውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚረዱ አራት የጥናት ሰነዶችን አስረከበ፡፡
ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የክልሉን ቱሪዝም ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚያስችሉ የቱሪስት ማፕ፣ የባህላዊ ምግብ ዝግጅት ጥናት፣ በአካባቢው የሚገኝ እምቅ የቱሪዝም ሀብት ጥናት እና የጉዞ ጥቅል ጥናትን የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምርና ማማከር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ሥዩም ለክልሉ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑሪ ከድር አስረክበዋል፡፡
በርክክብ መድረኩ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለን ጨምሮ ፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ባለሞያዎች ተገኝቸዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጠቀሙ

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et