በልምድ የተገኘን እውቀት እውቅና መስጠት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሲቪል ሰርቨስ ዩንቨርስቲ ለመጡ ሠራተኞች በልምድ የተገኘን እውቀት እውቅና መስጠት የሚያስችል የተግባር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የአጫጭር ትምርህርት ክፍል ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አሰፋ እንደተናገሩት ለ160 ሰልጣኞች በምግብ ዝግጅት በዳቦና ኬክ፣ በመስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና ሌሎች ተያያዥ ሙያዎች ለ15 ቀን የሚቆይ አጫጭር ስልጠና እየሰጡ እንደሆነ ገልጸዋል።
ሰልጠናው የረዥም ዓመት የሥራና ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች ልምዳቸውን በስልጠና ተቋማት አልፈው እውቅና እንዲያገኙ እና ደረጃ እንዲወጣለት የሚያስችል ‘በልምድ የተገኘን እወቀት እውቅና መስጠት’ (RPL) አሰራር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስለሆነም ሰልጣኞቹ ይህን የተግባር ስልጠና ከጨረሱ በኋላ ምዘና እንዲወስዱ በማድረግ የደረጃ ሁለት ሰርተፍኬት ባለቤት የሚሆኑ ሲሆን ፍላጎት ያላቸው ወደ ላይ ደረጃቸውን ለማሳደግ በስልጠና ተቋማት መቀጠል ይችላሉ ተብሏል፡፡
ይህ እውቅና በሁሉም በልምድ የተገኙ ሙያዎች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን እንደሆነ በቅርቡ ጸድቆ ወደሥራ የገባው የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ አሳውቋል፡፡