የዋና ዳይሬክተር መልዕክት
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዘርፉ ፈጣን እድገት እንዲመጣ፤ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ሰው ሃይል በማቅረብ፤ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የማማከር አገልግሎት በመስጠት ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው እድገት የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ የሚገኝ አንጋፋ ተቋም ነው፡: በአሁኑ ሰአት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍን ውጤታማ ለማድረግ ኢንዱስትሪው ከሙያ ደረጃ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ምዘና ባለው ሰፊ የስልጠና ሂደት ባለቤት ሆኖ የመሪነት ሚናውን መወጣት እንደሚጠበቅበት ይታወቃል፡፡