ፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
Federal Tourism Training Institute
We Strive for Excellence

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከማልታ ኤምባሲ ጋር ውይይት አካሄደ

March 17, 2026
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከማልታ ኤምባሲ ጋር ውይይት አካሄደ

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከማልታ ቱሪዝም ኢንስቲትዩት ጋር ከዚህ ቀደም ተጀምሮ የነበረን ግንኙነት ማስቀጠል በሚቻልባቸው የግንኙነት መስኮች ዙሪያ የኢንስቲትዩቱ ዋናዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና በኢትዮጵያ የማልታ ኤምባሲ ተወካይ አምባሳደር ዶ/ር ሪታ ቦኔሎ ውይይት አድርግዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ከማልታ ቱሪዝም ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከዚህ ቀደም መኖሩን ነገር ግን በሁኔታዎች አለመመቻቸት ወደሥራ አለመገባቱን አንስተው የተጀመሩ ግንኙነቶችን ማስቀጠልና በትብብር መስራት የኢንስቲትዩቱ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ዶ/ር ሪታ ቦኔሎ በበኩላቸው በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የአቅም ግንባታ፣ የልምድ ልውውጥ እና የእውቀት ሽግግር የመሳሰሉት ጉዳዮች በአዲስ መልክ ተዘጋጅተው በአፋጣኝ ወደ ሥራ መግባት እንደሚፈልጉ ገልጸው፤ የኢንስቲትዩቱን የተግባር ስልጠና ክፍሎችም ጎብኝተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የማልታ ቱሪዝም ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንስቲትዩቱን መጥተው መጎብኘታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Gallery image