ኢንስትቲዩቱ ከደባርቅ ዩንቨርሲቲ ጋር ተፈራረመ
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደባርቅ ዩንቨርሲቲ ጋር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደተናገሩት የስምምነቱ ትኩረትም በስልጠና በምርምርና በማማከር እንዲሁም በማህበረስብ አቀፍ አግልግሎቶች ላይ በደባርቅ ዩንቭርስቲ ያለውን እምቅ ሀብት በጋራ በመስራት ያላቸውን ልምድና እውቀት ተጠቅመው ለመስራት ነው ብለዋል፡፡
የደባርቅ ዩንቨረስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማው ዘገየ በበኩላቸው እንደገልጹት ተቋሙ ሆስፒታሊቲን በተላበሰ መልኩ ለተደረገላችው አቀባበል አመስግነዋል፤
ተቋማቸው በቱሪዝምና በግብርና እምቅ ሀብት ያለው በመሆኑ በጥናትና ምርምር ሥራዎች በተግባር የሠራተኛና ሰልጣኝ ልምድ ልውውጦችን ከቱሪዝም ማሰልጠኛ ጋር መስራት ከአንጋፋነቱ አንጻር ግዴታ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ተቋማት ለብቻቸው ከመስራት ይልቅ በጋራ መስራት እንደሀገር ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በአጭር ጊዜ ዝክረ ተግባር በማዘጋጅት ወደ ሥራ እንደሚገቡ ተገልጿል፡፡