በንብረት አስተዳደርና አወጋገድ እንዲሁም ኢ ፍሊት ማኔጅመንት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከፌዴራል የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመተባበር ስለ መንግስት ንብረት አስተዳደር እና አወጋገድ እንዲሁም e- Fleet ማንጅሜንት ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የተቋሙ የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ የመንግስት የንብረት አስተዳደር ፣ እንዲሁም አወጋገድ እና (e-Fleet Management) የመኪኖች ስምሪት ፣ ለጥገናና ነዳጅ አጠያየቅ ስልጠና መውሰዱ በኤሌክትሮኒክስ ሲስተም ተጠቅሞ አሰራርን ማዘመን ጊዜን፣ ሀብትን እንዲሁም ጉልበትን የሚቆጥብ በመሆኑን በአግባቡ መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከስልጠናው በኋላ የንብረት አወጋገድን ፣ የመኪና ስምሪት፣ ጥገናና ነዳጅ ጥየቃ ወደ ሲስተም እንደሚገባም ተገልጿል።
ስልጠናውን የሰጡት ከፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን አቶ ደበበ ማሞ እና አቶ ኃይለሚካኤል ብሩ ናቸው።