የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና ቱሪዝም በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ
ቱ ማ ኢ መጋቢት 12/2018 ዓ ም
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከክልል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ከተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና ቱሪዝም በሚል ርዕስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት አካሄደ።
በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ባስተላልፉት መልዕክት ኢንስቲትዩቱ በሚያከናውናቸው ተግባራት ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ጋር በቅርብ የሥራ ግ ንኙነት እንዳለው ገልጸው ዛሬ በተዘጋጀው የቴክኖሎጂ የስልጠና እና የምክክር መድረክ ኢንስቲትዩቱ ያለውን ለተሞክሮ ለማካፈል መዘጋጀቱን ይገልጸዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምርምርና ማማከር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የቱሪዝም ዘርፍ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን
ዲጂታል 2030 ኢትዮጵያ እውን ማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት መታቀዳቸውን እና ከነዚህ እቅዶች አንዱ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ከ ዲጂታል እቅዱ ጋር ለማስተሳሰር በተያዘው እቅድ ዙሪያ እንደ ኢንስቲትዩት መስራት ይጠበቅብናል ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል፡፡
አገራችን በቱሪዝም ዘርፍ በዓለም ቅርስነት ያስመዘገበቻቸው የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ፣ እንዲሁም በባህል፣ በታሪክና በተፈጥሮ አሟልታ የያዘች ከአፍሪካም ቀዳሚ መሆኗን እንዲሁም መንግስት ለዘርፉ እድገት የሰጠውን ልዩ ትኩረት እንደምቹ ሁኔታ ጠቅሰው ከዓለም ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ ያሉንን ሀብቶች ለማስተዋወቅና የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ የዲጂታል ቱሪዝም ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የሰለጠነ የሰው ሃይል ልማት ጋር በተያያዘ በስልጠና የተደገፈ የዲጂታል ኮርሶችን ማካተት፣ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በዘርፉ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ ካሉ ተቋማት ጋር ግንኙነትን ለማጠናከር እየሠራነው ብለዋል፡፡
በመድረኩ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ ልምድ ካላቸው ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት እና አቅምን ማሳደግ ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በቱሪዝም ዘርፍ ወጪ ቆጣቢ እና በሀገር ውስጥ መተካት የሚችሉ የጉዞ መሳሪያዎች ጥናት በኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዲን በአቶ ዳዊት ኃ/ሚካኤል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.etዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et