ፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
Federal Tourism Training Institute
We Strive for Excellence

ኢንስቲትዩቱ ያጠናቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ወደሥራ እንዲገቡ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

March 23, 2026
ኢንስቲትዩቱ ያጠናቸውን  የቴክኖሎጂ  ውጤቶች በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ወደሥራ እንዲገቡ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

ቱ ማ ኢ መጋቢት 13/2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በዘርፉ ያሉ የቴክኖሎጂ ፍላጎቶች ጥናት እና ከሀገራችን ዲጅታል 2030 ስትራቴጂ ካስቀመጠቻቸው ትላልቅ ግቦች ጋር በእጅጉ የሚጣጣሙ በራስ አቅም የሚለሙ፣ የሚሰፉ እና ወደሥራ መግባት የሚችሉ ነገር ግን በከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ የምናስመጣቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች መቀየር የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ይገኛል።
የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዲን አቶ ዳዊት ኃይለሚካኤል ያለሙት የአንላይን ፈተና ሥራ ላይ ከዋለ ሁለተኛ ዓመቱን የያዘ ሲሆን ሶፍትዌሩ ካሉት መገለጫዎች ሥራ ላይ ሲውል ያገጠሙ ችግሮችን እያሻሻለ በአሁኑ ጊዜ ከፈተና ስርቆት፣ ኩረጃ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የደህንነት ስጋት ነጻ የሆነ ሶፍት ዌር ለሌሎች ማዳረስ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አቶ ዳዊት ገልጸዋል፡፡
ተቋሙ በድጂታላይዜሽን ዙርያ የሰራቸው የተማሪዎች መረጃ ዲጂታላይዝ ሰርዓት፣ የትራንስፖርት መቆጣጠርያ እንዲሁም ከወረቅት ነፃ የኮሚዩኒኬሽን ሥርዓት ለተሳታፊዎች ልምድ አካፍለዋል፡፡
ስለሆነም ከቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ዲጂታል 2030 ጋር በተያያዘ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ቀርጾ እየተገበራቸው የሚገኙ የለውጥ እሳቤዎችን መሰረት በማድረግ በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ኢንስቲትዩቱ ጥሪ አቅርቧል በቀጣይ ለሚመለከታቸው ለአካዳሚክና የአይሲቲ ባለሞያዎች ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል ፡፡
በጥናቱ ውጤት መሰረት የቱሪዝም ዘርፉ እድገት በቴክኖሎጂ ላይ መሰረት ያደረገ በመሆኑ ከ36 በላይ የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች፣ ዲኖች እና የሆቴልና ቱሪዝም ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም ያላቸውን ፍላጎት እና ወደተግባር መግባት በሚቻልበት ሁኔታ ተወያይተዋል ፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም፡ https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et