ፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
Federal Tourism Training Institute
We Strive for Excellence

ኢንስቲትዩቱ እያዘጋጀ ያለው የቱሪዝም መዝገበ ቃላት በባለድርሻ አካላት ተገመገመ።

March 25, 2026
ኢንስቲትዩቱ እያዘጋጀ ያለው የቱሪዝም መዝገበ ቃላት  በባለድርሻ አካላት ተገመገመ።

ቱማኢ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር እያዘጋጀ ያለውን የቱሪዝም መዝገበ ቃላት በዘርፉ ለሚገኙ የቱሪዝም ፣ ሆቴል ባለሙያዎች የማህበራት ኃላፊዎችና የቱሪዝም ጋዜጠኞች በተገኙበት የመጀመሪያ ዙር ግምገማ አደረገ።
ኢንስቲትዩቱ 4000 የቱሪዝም እና የሆስፒታሊቲ ቃላት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ፍቺ የተዘጋጀላቸው መሆናቸው ተገልጿል።
መድረኩን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እና በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችእና ባህሎች ጥናት ዳይሬክተር ዶ/ዮሀንስ አድገህ መርተውታል።
የተሰራው የሙዳዬ ቃላት ወይስ መዝገበ ቃላት ፍቺ ከሚል ጀምሮ ከአማርኛ ቋንቋ የማይገልፃቸው ከሙያው ባህሪ ያሉ ቃላት ፍቺዎች እንዴት እንደታዩ የሚያጠይቁ ሃሳቦች ከተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በጥናቱ የቱሪዝምና የሆቴል አሰልጣኞች እንዲሁም በሙያቸው ከኢንደስትሪው ጋር በቅርበት እየሰሩ የሚገኙ ባለሙያዎች እየተሳተፉበት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የተሰጡ አስተያየቶች ተካተውበት ቀጣይ የማጠቃለያ መድረክ እንደሚኖር ተገልጿል።
ኢንስቲትዩቱ የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ፍቺ ሥራ ከጀመረ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም፡ https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official
ዌብሳይት፡ https://www.tti.edu.et