6ኛው ቱሪዝምና አንግዳ ተቀባይነት ሳምንት ከግንቦት 5 _9 2010
Description
የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት(ሆ.ቱሥ.ማ.ኢ.)በሀገራችን የሆቴልና ቱሪዝም
ኢንዱስትሪ እንዲፈነጥቅ ፋና ወጊ የሆነ የመጀመሪያው የመንግስት ተቋም ነው፡፡ ይህ ተቋም
ከተመሠረተበት ከ1961 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 49 አመታት እንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው
ኃይል በማሰልጠንና በማቅረብ በሀገራችን በመሪነት ከሚገኙት የአገልግሎት ዘርፎች አንዱ የሆነውን
የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ የላቀ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
ይህ አንጋፋና ፋና ወጊ የማሰልጠኛ ተቋም መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት በሚኒስትሮች ምክር
ቤት ደንብ ቁጥር 174/2002 ዓ.ም በአዲስ መልክ ተቋቁሞ ተገቢውን ትምህርትና ሥልጠና፣ ጥናትና
ምርምር እና የማማከር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
Uploaded on: May 28, 2026 12:25