'መልካምነት ተመሰገነ ቱ.ማ.ኢ
'ሚያዝያ 30/2018ዓ.ም
የቀድሞ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የቀለምና የስነምግባር መምህራችን ናቸው ያሏቸውን የኢንስቲትዩቱ የቀድሞ የፈረንሳይኛ ቋንቋ መምህር አቶ ሳምሶን መንገሻ (መስዬ ሳምሶን) ለመልካምነታቸውና በህይወታቸው አርአያ ስለሆኗቸው የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጁ ።
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በምስጋና ፕሮግራሙ ተገኝተው እንደገለጹት አቶ ሳምሶን የቀድሞ መምህራቸው በኋላም የሥራ ባልደረባ ሆነው አብረው መስራታቸውን ገልጸው ትውልድ ላይ የሠሩት ሥራ እንዲህ ለምስጋና መብቃቱ በጣም መደሰታቸውን ገልጸዋል።
አቶ ሳምሶን የኢንስቲትዩቱ አንጋፋ አሰልጣኝ ለሥራቸው ካላቸው ፍላጎት የተነሳ የጡረታ ጊዜያቸው ከደረሰ በኋላም በራሳቸው ፍላጎት ተጨማሪ ክፍያ ሳይጠይቁ ከ10 ዓመታት በላይ በበጎ ፈቃዳቸው ለትውልድ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተዋል።
መስጠት መታደል ነው ፤ ከማስተማር ባሻገር ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ከማስቀጠል አኳያ ወሰንም መጠንም የሌለው መልካምነት ሰጥቶናል ብለዋል የቀድሞ ተማሪዎቻቸው።
ፕሮግራሙን ያስተባበሩ እና ያዘጋጁት የኢንስቲትዩቱ የቱር ጋይድና የቱር ኦፕሬሽን የቀድሞ ተማሪዎች ሲሆኑ በፕሮግራሙ ምስክርነት ከሰጡት አቶ ሳምሶን መምህር ብቻ ሳይሆን እንደ አባት የሚከታተል፣ የሚቆጣጠር ፣ምንቸገረህ የሚል እና እንደጓደኛ የሚቀርብ ነበር ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
የፈረንሳይኛ ቋንቋን ሲጀምሩት ፈርተው ሲጨርሱ ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንደ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ቋንቋ ሳይሆን እንደ አፍመፍቻ ቋንቋ እንዲወዱት እንዲነጋገሩበት እድል እንደፈጠራላቸው በአስጎብኚነት ሥራ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ አስጎብኚ የሆኑ በርካታ እንደሆኑም በምስጋና ፕሮግራሙ ተገልጿል።
በመጨረሻም የቀድሞ ተማሪዎቻቸው የማሰታዎሻ ስጦታ አበርክተዋል።
መልካምነት " ለራስ እንደሚቀቡት ሽቶ ነው ወደዱም ጠሉሙ ለሌሎች የሚሸት ፣ የሚጋባነው ብለውታል" እኛም መልካም ሥራ ለራስ ፣ ለውስጥ ሰላም ነው በማለት አቶ ሳምሶን ስለሰጡን መልካም ነገር ፕሮግራሙን ያዘጋጁትንም እናመሰግናለን።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less