ኢንስቲትዩቱ የቴክኒካል አማካሪ ቦርድ አባላትን አመሰገነ
ቱ.ማ.ኢ
ሰኔ 8/2018 ዓ.ም
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢንስቲትዩቱ የቴክኒካል አማካሪ ቦርድ አባላት በመሆን ያገለገሉ ባለሙያዎችን የሥራ ዘመን መጠናቀቅን በማስመልከት የተከናወኑ ሥራዎች አፈፃጸም እና የእውቅና መርሃ-ግብር አካሄዷል።
የማጠቃለያና የእውቅና መርሃ-ግብሩን በንግግር የከፈቱት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት፤ ተቋሙ በምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ማሳደጊያና ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት (EASTRIP) ውስጥ አባል ተቋማት አንዱ ሆኖ ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስኬታማና ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸው፤ ለዚህም ስኬት የቴክኒካል አማካሪ ቦርዱ የነበረው ሙያዊ ድጋፍ የጎላ ድርሻ እንደነበረው አስምረውበታል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ኢንስቲትዩቱ ወደ EASTRIP ፕሮጀክት የገባው ከሌሎች ተቋማት ዘግይቶ የነበረ ቢሆንም፣ በቦርዱና በሠራተኞች የተቀናጀ ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።
የቴክኒካል ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ መልካሙ መኮንን በበኩላቸው በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ይህንን ኃላፊነት ሰጥቶ በፕሮጀክቱ ጥቂት ሙያዊ አበርክቶ እንዲኖራቸው ዕድል ስላመቻቸላቸውና ላደረገላቸው እውቅና ለኢንስቲትዩቱ ያላቸውን ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
በዕለቱ በተካሄደው መርሃ-ግብር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አብርሃም ለገሰ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን፣ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የተገኙ ውጤቶችን በዝርዝር የሚያሳይ የአፈፃጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በተነሱ ነጥቦች ላይም ውይይት ተደርጓል።
ይህ የእውቅና መርሃ-ግብር ተቋሙ ለባለሙያዎቹ ያለውን ክብር የገለጸበት መሰል ሀገራዊና ቀጠናዊ ፕሮጀክቶችን በላቀ ስኬት ለማስቀጠል ያለውን ዝግጁነት ያሳየበት ሆኖ ተጠናቋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less