የኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች በአንድነት ፓርክ እና በብሔራዊ ቤተመንግሥት፤
ቱ.ማ.ኢ
ግንቦት 20/2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በየዓመቱ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሰልጣኞች በንድፈሃሳብ የቀሰሙትን እውቀት በተግባር ለመደገፍ የሚያስችል ትምህርታዊ ጉብኝት ከሚወስዱባቸው መዳረሻዎች ለህዝብ ክፍት የተደረጉት አንድነት ፓርክና ብሔራዊ በተመንግስት ይጠቀሳሉ፡፡
እነዚህ መዳረሻዎች አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የታሪክ፣ የተፈጥሮና የባህል ቅርሶችን የያዙ በመሆናቸው ለሰልጣኞቻችን ጥሩ እድል ፈጥሯል ያሉት የጉብኝቱ አስተባባሪና የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ሲሳይ አብርሃም ናቸው፡፡
አቶ ሲሳይ ስለጉብኝቱ ዓላማ ሲገልጹ ሰልጣኞች ተግባራዊ እውቀት በመቅሰም የሀገራችንን ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህቦች አያያዝና አደረጃጀት በቅርብ እንዲረዱ ማስቻል፤ በፓርኮችና በቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተግባር ማየትና ያሉ ከክፍተቶች በስልጠና መግደገፍ እንዲሁም የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ነገ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ለዓለም የሚያስተዋውቁ ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት ነው ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ሰልጣኞቹ የሀገሪቱን አስደናቂ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የተፈጥሮ ሃብቶች እና የቤተመንግሥቱን ልዩ የስነ-ህንጻ ጥበብ በጥልቀት የተመለከቱ ሲሆን ይህም ለቀጣይ ሙያዊ ጉዟቸው ትልቅ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less