ፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
Federal Tourism Training Institute
We Strive for Excellence

የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞውን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ሰርተው አስተዋወቁ።

April 23, 2026
የኢንስቲትዩቱ  ባለሙያዎች የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞውን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን  ሰርተው  አስተዋወቁ።

ቱ .ማ. ኢ ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የወረቀት ምልልስን የሚያስቀሩ ዲጂታል በሆነ መንገድ ሥራን የሚያቀላጥፉ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞውን የሚያፋጥኑ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ተሰርተው የሙከራ ትግበራቸውን ለሰራተኛው አስተዋውቀዋል፡፡
ከአጥኚዎቹ አንዱ አቶ ደስይበለው አግማስ እንዳቀረቡት የተቋሙን የውስጥ አሰራር ዘመናዊ ለማድረግ በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ሥራዎች መስራታቸውን ገልጸው በዋነኝነት የሰነዶች ቁጥጥር ማዕከል (Digital Documents Control Center System) ሰነዶች ሳይጠፉና ሳይበላሹ በአንድ ማዕከላዊ ሰርቨር ላይ እንዲቀመጡ ያደርጋል፣ የተራቀቀ የፍለጋ ዘዴን በመጠቀም መረጃን በሰከንዶች ውስጥ ለማግኘት ያስችላል ብለዋል።
ሌላኛው አጥኚ በአቶ ሚሊዮን ጸጋዬ የተሰራው የኮምፒውተርና ኢንተርኔት ጥገና እና መሰል አገልግሎቶች የሚፈልግ የውስጥ ሰራተኛ ወይም የሥራ ክፍል ጥያቄውን በቀላሉ ማቅረብና ፈጣን ምላሽ ለማግኘት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የውይይት መድረኩን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞችና አሰልጣኞች ተገኝተው ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን ሰጥተዋል ለተሰራው ሥራም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official