በመረጃ አያያዝ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በሚል የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ተጎበኘ። ቱ ማ ኢ
ግንቦት /2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል የሚያሳይ ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል።
መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው።
መረጃ የተዋሰ ወይም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ ሀገራዊ አጃንዳን ለማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው ተብሏል።
በኤግዚብሺኑ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት መሰራቱ ለየት ያደርገዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን እንዳለበት በባለሙያዎቹ ተገልጿል።
ኤግዚቢሽኑን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ኤጄንሲ እና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ናቸው።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less