ፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
Federal Tourism Training Institute
We Strive for Excellence

ስልጠና ከወሰዱት 139 የልምድ ባለሙያዎች 124 ያህሉ በጥሩ ውጤት አለፉ

April 29, 2026
ስልጠና ከወሰዱት 139 የልምድ ባለሙያዎች 124 ያህሉ በጥሩ ውጤት አለፉ

ቱ. ማ. ኢ
ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር በምግብ ዝግጅት፣ በእንግዳ አቀባበልና በመስተንግዶ፣ በቤት አያያዝ እና በዳቦና ኬክ ዝግጅቶች ለአንድ ወር ያህል ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ ምዘና በመስጠት አጠናቋል።
የአጫጭር ስልጠና ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አሰፋ ስልጠናው በሥራ የተገኘን ዕውቀት አጫጭር ስልጠና ሰጥቶ በመመዘን ወደ ደረጃ ለመቀየር የሚያስችል ሲሆን ከ139 ሰልጣኞች መካከል 124 የሚሆኑት ተመዝነው በጥሩ ብቃት አልፈዋል ብለዋል፡፡ ምዘናውን ያላላፉ 15 የሚሆኑት ሰልጣኞች በቀጣይ ራሳቸውን በማብቃት ድጋሚ መመዘን የሚችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን ሲወስዱ የነበሩ ሰልጣኞች በልምድ ሲሰሩ ከነበረው በዘርፉ ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና እጅግ እንደጠቀማቸው፤ ጉልበት ከሚያደክም ሥራ የተሻለ፣ ጊዜና ገንዘብ ሊቆጥብ የሚችል አሰራር እንደሰለጠኑም ገልጸዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official