" ከራስ ደጀን እስከ ዳሎል የማይበገር ቱሪዝም ኮሪደር ለመገንባት የሚያስችል " የሶስትዮሽ አውደ ጥናት ተካሄደ።

July 06, 2026
" ከራስ ደጀን እስከ ዳሎል  የማይበገር ቱሪዝም  ኮሪደር ለመገንባት የሚያስችል " የሶስትዮሽ አውደ ጥናት ተካሄደ።

ቱ ማ ኢ
ሰኔ 27/2018 ዓ ም
የፌደራል ቱሪዝምና ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት፣ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ (እና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ከራስ ደጀን እስከ ዳሎል የማይበገር ቱሪዝም ኮሪደር ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ሥራዎች ላይ ያተኮረ የሶስትዮሽ አውደ ጥናት አካሂደዋል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሀመድ ዑስማን የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የመድረኩን አስፈላጊነት አስገንዝበዋል።
ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ፕሮፌሰር አለማየሁ ቢሻው ሁለቱን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መዳረሻዎች (ራስ ደጀንን እና ዳሎል) በቱሪዝም ልማት ማስተሳሰር በሚቻልባቸው ወሳኝ ነጥቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንደስትሪ አሁናዊ እይታና የወደፊት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ ከሶስቱም ተቋማት የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎችና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፣ የሀገሪቱን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ በምርምርና በጋራ ትብብር ለማሳደግ ግልጽ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less