የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 13ኛው የቱሪዝም እና መስተንግዶ ሳምንት ፓናል ውይይት

July 02, 2026
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 13ኛው የቱሪዝም እና መስተንግዶ ሳምንት ፓናል ውይይት

ቱ ማ ኢ
ሰኔ 24/2018 ዓ ም
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በየዓመቱ የሚያዘጋጀውና ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ያለው የቱሪዝም እና መስተንግዶ ሳምንት ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በፓናል ውይይት ቀጥሎ ውሏል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በፓናል ወይይት መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የቱሪዝም ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚና ገፅታ ግንባታ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ የጠቀሱ ሲሆን፣ ኢንስቲትዩቱ ከነባራዊው የሀገሪቱ የቱሪስት መዳረሻዎች ልማት ፍጥነት ጋር የሚመጣጠንና በክህሎቱ የላቀ የሰው ኃይል ለማፍራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ ጥናትና ምርምር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም በበኩላቸው የቱሪዝም እና የመስተንግዶ ሳምንት በዘርፉ ያሉ ተዋናዮች የሚገናኙበት፣ ተጨባጭ ችግሮችን በጥናትና ምርምር ላይ ተመስርተው የሚወያዩበትና የጋራ አቅጣጫ የሚቀይሱበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
የዘንድሮው የፓናል ውይይት ትኩረት “የክህሎት ልህቀት ለቱሪዝም ልማት” በሚል መነሻ ሀሳብ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣
የፓናል ውይይቱ አስተናባሪ አቶ አለማየሁ ፍቅረማርያም በመግቢያቸው " ቱሪዝም ተወዳዳሪ የሚሆነው ውብ መዳረሻዎች ብቻ ስላሉት አይደለም ፤ ይልቁንም ድንቅ የሰው ሃይል ሲኖረው ነው" ሲሉ የጉዳዩን አስፈላጊነት አብራርተዋል።
በዋናነት በሚከተሉት ሶስት ቁልፍ ጉዳዮች ላይም ሰፊ ውይይት ተደርጓል፦
1.የቱሪዝም መሠረተ-ልማት ግንባታ ፍጥነት እና የሰው ኃይል አቅርቦት ማመጣጠን፣
2.በሀገሪቱ እየተገነቡ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና ፕሮጀክቶች ካላቸው ፈጣን የእድገት ፍጥነት ጋር አብሮ የሚራመድ፣
3.የዘመኑን የገበያ ፍላጎት ያገናዘበና ብቁ የሰው ኃይል በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት በማፍራት ረገድ ያሉበት ተጨባጭ ሁኔታዎች ተገምግመዋል።
የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር
በዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ ኢንዱስትሪው (የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የግል ባለሀብቶች)፣ ማሰልጠኛ ተቋሙ እና መንግስት በምን መልኩ ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸውና የተቀናጀ አጋርነትን መፍጠር በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ጥልቅ ምክክር ተደርጓል።
የክህሎት ልህቀትን ማረጋገጥ በየደረጃው የሚሰለጥኑ ባለሙያዎች በንድፈ-ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ የክህሎት ልህቀት (Skill Excellence) የበለፀጉ እንዲሆኑ ተቋማዊ አቅምን ለማሳደግ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል ።
ፓናሊቶቹ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያካበቱ ባለሙያዎች ናቸው።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less