ኢንስቲትዩቱ ከአማዴየስ (የጉዞ ቴክኖሎጂ ኩባንያ) የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድረገ፡፡
ሚያዝያ 15/ 2018 ዓ.ም.
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና ከአማዴየስ የኢትዮጵያ ተወካይ / ቦስተን ፓርትነርስ ኃ/የተ/የግ/ማ እና አባላቱ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ጠቃሚ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ አማድየስ ለቱሪዝም ማሰልጠኛ ማበርከት ስለሚችለው አስተዋጻኦ እና የሚሰጠው አገልግሎት ከሌሎች ሶፍትዌሮች የሚለየው ምን እንደሆነ እና ሌሎች ነጥቦችን በጥያቄ መልክ አቅርበው ከተወካዮቹ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
አማዴየስ (www.amadeus.com) በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የጉዞ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን፣ የአየር ትኬት፣ የሆቴል፣ የመኪና እና የባቡር ጉዞ ዝርዝርና ዋጋ ማየት፣ ቦታ ማስያዝ እና ትኬት መቁረጥ የሚያስችሉ ዘመናዊ እና የተቀናጀ የጉዞ ቴክኖሎጂዎችን የሚያቀርብ ኩባንያ ነው።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official