ኢንስቲትዩቱ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ሚያዝያ 2018 ዓ.ምየፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ኢንስቲትዩቱ እና ዩንቨርሲቲው አብረው ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰው
በቱሪዝም እና በሆቴል ዘርፍ በስልጠና በጥናትና ምርምር እና የማማከር አገልግሎት የሚሰጥ አንጋፋ ተቋም መሆኑን እና
ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተደረገው ስምምነት የተቋሙን ተልዕኮ በማከናወን ሂደት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ በበኩላቸው የአማራ ክልልና በተለይም ባሕር ዳር ከተማና አካባቢው ያለውን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ ለማልማትና ለመጠቀም ይህ ስምምነት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው ፣ ለትግበራውም ዩኒቨርሲቲው ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ፊርማውን የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩምና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ፈርመውታል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official