በአሜሪካ የኢትዮ-ቴክሳስ “ፊውዥን” ባርቤኪው ባለቤቶች ለኢንስቲትዩቱ ሰልጣኞች ልምድ አካፈሉ፡፡
ቱ.ማ.ኢ
ግንቦት 2018ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአሜሪካ ኤምባሲ አስተባባሪነት የአሜሪካን 250ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ዓመቱን ሙሉ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የምግብ ዝግጅት (Smoke'N Ash BBQ) ባለቤቶች የሆኑትን ፓትሪክ እና ፋሲካ ሂክስን ከተቋሙ ሰልጣኞች ጋር የአሜሪካን ምግብ በኢትዮጵያ ቅመማቅመም እና እንጀራ ሰርቶ እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል አሳይው ልምድም አካፍለዋል።
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንግዶቹን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ በሀገራት መካከል ከሚደረጉ ግንኙነቶች ለማጠናከር ይህን መሰል ዓውድ ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡
በአሜሪካ ኤምባሲ በኩል የልኡካን ቡድኑን የመሩት ሚስ ኤድሪያን ቢ ኑትዝማን የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ካውንስለር እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ አንጋፋ እንደሆነ እና የተቋሙ ሰልጣኞች ከአሜሪካ የምግብ ባለሙያዎች ጋር አብሮ የመስራት እድል መፈጠሩ እንዳስደሰታቸው ገልጸው፤ የምግብ ዝግጅቱ ዓላማ ምግብ በሥራ ፈጠራ እና በጋራ እሴቶች አማካኝነት ሁለቱን ሀገራት ለማቀራረብ እድል ይሰጣል ብለዋል፡፡
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less