በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ አቅሞችን አሟጦ ለመጠቀም ተቋማት ተቀናጅተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ተባለ።
ቱ.ማ.ኢ
ሚያዚያ 25/218 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የዩንቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በዘርፉ የሚገባውን ጥቅም ለማግኘት በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ታግዘው ሁለቱ ተቋማት ቢሰሩ እንደሀገር በዘርፉ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።
በጥናትና ምርምር ጉባኤው ከቀረቡ የጥናት ወረቀቶች አንዱ በሲዳማ ክልል ያለውን የምግብ ቱሪዝም ሀብት የሚያሳይ ሲሆን በሚገባ ማስተዋወቅና ክልሉም ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ የሚዳስስ ነው።
አጥኚው የኢንስቲትዩቱ አሰልጣኝ ጌትሽ ገደፋው ሲሆኑ በገለፃቸው በዓለም ላይ በምግብ ቱሪዝም የሚታወቁ ከተሞችን እንደምሳሌ አቅርበዋል።
ሌላው የጥናት ጽሑፍ አቅራቢ ከወልዲያ ዩንቨርስቲ አቶ ጌታቸው ከበደ 'Reimagining Tourism as Catalysts for Ethiopia 's Multi_Sectoral Transformation in the Digital Era' በሚል ርዕስ እና ሌሎች ሁለት የጥናት ወረቀቶች ቀርበዋል።
በመጨረሻም ለጥናቱ ተሳታፊዎች እና አስተባባሪዎች የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና የዩንቨርሲቲው ም/ፕሬዚዳንት የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official