የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ በዓለማችን እጅግ ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ ከመጡ የሥራ መስኮች አንዱ መሆኑ ተገለጸ።
ቱ ማ ኢ
ሚያዝያ 24/2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር "የፈጠራና ኢኖቬሽን ቀጣይነት ላለው የቱሪዝም ልማት"በሚል መሪ ሀሳብ የተለያዩ ምርምር ሥራዎች ቀርቦ ወይይት ተደርጓል።
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በመክፈቻ ፕሮግራሙ እንደገለፁት የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ በዓለማችን እጅግ ከፍተኛ ትኩረት እያገኙ ከመጡ የሥራ መስኮች አንዱ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው ተጨባጭ እድገት በማስመዝብ ላይ የሚገኝ ዘርፍ ነው፡፡
በርካታ ጥናቶች እንደያሚያረጋግጡት፣ ዘርፉ ለበለፀጉትም ሆነ ለታዳጊም አገራት ሰፊ የሥራ እድል በመፍጠር እና የውጪ ምንዛሪ ገቢን በማስገኘት ሁነኛ የሀገራዊ ሀብት ምንጭ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም፣ አሁን በደረስንበት፣ ዘመን የቱሪዝም ዘርፉ፣ ከማህበራዊ ወደ ኢኮኖሚ ሴክተር ብሎም ወደ ዲጂታል ቱሪዝም በመሸጋገር ላይ የሚገኝ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሆኖ እየመጣ በመሆኑን ዘርፉ ለሰዎች በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን ከማስገኘት በዘለለ በሕዝቦች መካከል መልካም የኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ ግንኙነት እንዲሁም የባህል ትስስር እንዲጠናከርና እንዲጎለብት ለማድረግ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተናግረዋል ፡፡
የሀዋሳ ዩንቨርስቲ ዋና ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በበኩላቸው እንደገለፁት ሁለቱም ተቋማት እንደዚህ አይነት የምርምር ሥራዎች አብሮ መስራት ለሀገር እድገት ወሳኝ ለተቋማትም ጠቃሚ መሆኑን እና ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገትና ለሥራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
በመሪ ቃሉ መነሻነት በዘርርፉ ምሁራን አራት የጥናት ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official