13ኛው የቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት ተጠናቀቀ።
ቱ.ማ.ኢ
ሰኔ 25/2018 ዓ.ም
13ኛው የቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት «የላቀ ክህሎት ለቱሪዝም እድገት» በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቶ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
የበዓሉን መዝጊያ አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሳምንቱ እጅግ ፍሬያማና በርካታ ተሞክሮዎች የተቀሰሙበት እንደነበር ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ "ከሁሉ በላይ ይህ ሳምንት ትልቅ ትስስር የፈጠረ እና ብዙ ነገሮችን ያስተማረን ሆኖ አልፏል።
በተለይም በዘመናዊው ዓለም ቴክኖሎጂ እና የቱሪዝም ዘርፍ የማይነጣጠሉ በመሆናቸው፣ ለቴክኖሎጂ ትግበራና ፈጠራ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባን በተግባር ያሳየ መድረክ ነው" ብለዋል።
የቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት በተለያዩ ዘርፎች ተከፋፍሎ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የፈጠራና የክህሎት ማሳያ ኤግዚቢሽኖች፣ የጆፕፌር እና የተለያዩ የዘርፉ ሙያዊ ውድድሮች፣ በወቅታዊና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የፓናል ውይይቶች፣ ሰብዓዊነትን በተግባር ያሳየ የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው።
ዋና ዳይሬክተሩ ይህ ታላቅ ሳምንት በታሰበው ልክ በስኬት እንዲጠናቀቅ ሌት ተቀን የደከሙትን፣ ያቀናጁትንና የተሳተፉትን ተቋማትና ግለሰቦች በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ በተለያዩ የክህሎትና የፈጠራ ውድድሮች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተሳታፊዎች ላበረከቱ አስተዋጽኦ የእውቅና እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less