የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 13ኛውን የቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት እያከበረ ይገኛል።

July 01, 2026
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 13ኛውን የቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት እያከበረ ይገኛል።

ቱ. ማ. ኢ
ሰኔ 23/2018 ዓ ም
13ኛውን ቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ተሻለ በሬቻ የዘርፉ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የቱሪዝምና መስተንግዶ ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለገፅታ ግንባታ ያለውን ከፍተኛ ሚና አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው የክህሎት ልማት አስፈላጊነት በዘርፉ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማሟላት ኢንስቲትዩቱ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለእንዲህ አይነት መርሃ-ግብሮችና ለክህሎት ልማት የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ተማሪዎች፣ ባለሙያዎችና የዘርፉ ተዋናዮች በዚህ ሳምንት በሚቀርቡ ክነዋኔዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉና ልምድ እንዲለዋወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ለሰልጣኞች፣ ለኢንዱስትሪ አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሙሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት ዓላማ የሰልጣኞችን የፈጠራ ሥራዎችና ክህሎቶች ለማሳየት፣ የቅጥር ትስስር ለመፍጠር እና ከኢንዱስትሪው አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ በየጊዜው ራሱን በማደስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና በገበያው ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት ቁርጠኛ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በፕሮግራሙ በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ እና ቴክኖሎጂ ጥናቶች ውድድሮች ተካሂደዋል።
የ13ኛው ቱሪዝምና መስተንግዶ ሳምንት ክብረ በዓል የተለያዩ አውደ ርዕዮች፣ የሙያ ውድድሮች፣ የደም ልገሳ ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን የፓናል ውይይቶችን በማካተት በነገው እለት ፍፃሜውን ያገኛል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less