የቱሪዝም ዘርፉን የሰው ኃይል ብቃት ለማሳደግ የሚከናወኑ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡
ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት “የላቀ ክህሎት ለቱሪዝም እድገት” በሚል መሪ ቃል የሚያካሂደውን 13ኛውን የቱሪዝምና የመስተንግዶ ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)፤ የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ የኢኮኖሚ ምሰሶ እና የሀገር ገጽታ መገለጫ መሆኑን ገልጸው፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን ለመቅረፍ መንግሥት ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።
ተቋሙ ላለፉት አምስት ዓመታት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሥር መሆኑን ተከትሎ ሥልጠናዎቹ ፍላጎት መር እንዲሆኑ መደረጉንና ከሀገር ውስጥ ባለፈ ለውጭ ሀገራት ገበያ የሚሆን ብቁ የሰው ኃይል በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ጠቁመዋል።
የተቋሙ ጥናት እንደሚያሳየው በኢንዱስትሪው ውስጥ ካሉ ሠራተኞች መካከል 40 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በዘርፉ የሠለጠኑ በመሆናቸው፣ ክፍተቱን ለመሙላት አዲስ ሰልጣኞችን ከኢንዱስትሪው ጋር በትብብር ማሰልጠን እንዲሁም በሥራ ላይ ያሉትን በሥራ ላይ ሥልጠና (On-job training) ማብቃት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የፌደራል ቱሪዝም ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው፤ ተቋሙ በዘርፉ በርካታ ባለሙያዎችን በማፍራት ለኢንዱስትሪው ዕድገት የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝና በቀጣይም ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የመስተንግዶ ሳምንት መከበርም የሰለጠነው የሰው ኃይል ከኢንዱስትሪው ጋር በቀጥታ ለማገናኘት እንዲሁም ለዘርፉ ዕድገት ጠቃሚ ግብዓቶችን ለመሰብሰብ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።
ሰኔ 23/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI See less