በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት "የላቀ ብቃት ለዘላቂ አገራዊ የቱሪዝም ልማት"

July 01, 2026
በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት "የላቀ ብቃት ለዘላቂ አገራዊ የቱሪዝም ልማት"

በሚል መሪ ኀሳብ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ሙያዎች የክህሎት ውድድር የታጀበው ዓመታዊ የእንግዳ ተቀባይነትና የመስተንግዶ ሳምንት በዓል መከበር ጀመረ።
ዛሬ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም በገነት ሆቴል በይፋ የጀመረው በዓል
በተቋም ደረጃ ሲከበር የአሁኑ ለ13ኛ ጊዜ ነው።
የእንግዳ ተቀባይነትና የመስተንግዶ ሳምንት በዓል አከባበር ዋና ዓለማ፣ መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፉ ልማትና ዕድገት በሰጠው ልዩ ትኩረት፣ ሀገራችን በአፍሪካ ቀዳሚና ተመራጭ የቱሪስት መደረሻ እየሆነች በመምጣቷ፣ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች፣ ለደንበኞቻቸው በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ተወዳዳሪ የሆነ አገልግሎት ለመስጠጥ ይችሉ ዘንድ ዋና ትኩረታቸውን በሰው ሀይል ልማት ላይ እንዲያደርጉ ለማነሳሳት መሆኑ ተነግሯል።
ዛሬ እና ነገ በሚከናወነው ዓመታዊ የቱሪዝምና የመስተንግዶ ሳምንት መርሐግብሮች መካከል በመምህራን መካከል በሁለት ሙያዎች ማለትም በተግባራዊ ምርምር እና በቴክኖሎጂ ሽግግር እንደዚሁም በሰልጣኞች መካከል፣ በስድስት ሙያዎች ማለትም በኩሊነሪ ኣርት ወይም በምግብ አሰራር ጥበብ፣ በምግብና መጠጥ መስተንግዶ፣ በዳቦና ኬክ ፕሮዳክሽን፣ በፍሮንት ኦፊስ/በእንግዳ አቀባበል፣ በቱርጋይድ እና በቱር ኦፕሬሽን፣ ዙሪያ በተወዳዳሪዎች መካከል ይደረጋል። በተጨማሪ የቆዩ የክህሎት ውድድሮችን መሠረት በማድረግ የማጣሪያ ውድድሮችን አልፈው ለማጠቃያ ምዕራፍ በበቁ ተወዳዳሪዎች መካከል በሚደረግ ውድድር ፕሮግራሙ በእውቅና አሰጣጥ ሂደት የሚጠናቀቅ ሲሆን የማጣሪያ ሂደቱን ያለፉ 29 ሰልጣኞች እና 10 አሰልጣኞች በድምሩ 39 ተወዳዳሪዎች የማጠቃለያ ውድድሩ ተሳታፊዎች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ፣ የክህሎት ውድድሩና የመስተንግዶ ሳምንት አከባበር በዓሉ በርካታ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ተዋናዮች በሚሳተፉበት በፓናል ውይይት፡ በኤግዝብሽንና ፌስቲቫል እንደዚሁም በሥራ አውደርዕይ (ጆብፌር) እንደሚከናወን ተገልጿል።
በበዓሉ መክፈቻ መርሐግብር ላይ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ስለሺ ግርማ፤ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ፣
ወ/ሮ ነቢያ መሓመድ፣ የሥራና ክህሎት ሚ/ር፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራሮች፣ የፌዴራል ተቋማት የመንግሥት የሥራ ኋላፊዎች፣ የሆቴል ድርጅት ባለቤቶች እና የማህበሩ ተወካዮች፣ የልዩ ልዩ ሙያ ማህበራት አመራሮችና ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።#ድሬቲዩብ See less