በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ እና የጥቅም ግጭት በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።
ሰኔ 26/2018 ዓ ም
ቱ ማ ኢ
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በሥነ-ምግባራዊ ውሳኔ እና የጥቅም ግጭት በሚል ርዕስ ለተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በሥልጠናው መክፈቻ እንደገለጹት ተቋሙ የያዛቸውን ሀገራዊ የልማትና የማሰልጠን ግቦች በስኬት ለማሳካት የሥነ-ምግባር መርሆችን በጥብቅ መከተልና የጥቅም ግጭቶችን ቀድሞ መከላከል ወሳኝ ነው ብለዋል ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፣ እያንዳንዱ የሥራ ኃላፊና ሠራተኛ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ ተቋማዊና ሕዝባዊ አመኔታን በሚያጎለብት መልኩ በግልጽነትና በታማኝነት መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።
ሥልጠናውን የሰጡት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ሥራ አስፈፃሚ አቶ በጋሻው ቅጣው ሲሆኑ፣ በሥራ ቦታ ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ የጥቅም ግጭት አይነቶች፣ እነዚህን ግጭቶች እንዴት መለየትና ማስተዳደር እንደሚቻል እንዲሁም በሥነ-ምግባራዊ እሴቶች ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ስለሚገነባበት ሁኔታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ ሥልጠናው ተቋማዊ አሠራርን ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው ተገልጿል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less