ፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
Federal Tourism Training Institute
We Strive for Excellence

ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት'ፈጠራ ፣ ዘላቂነት እና ዘመናዊነት' መቀናጀት አለባቸው ተባለ።

May 04, 2026
ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት'ፈጠራ ፣ ዘላቂነት እና ዘመናዊነት' መቀናጀት አለባቸው ተባለ።

ቱ.ማ.ኢ
ሚያዝያ 25/2018 ዓ ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው 15ኛው የጥናትና የምርምር ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቱሪዝም ልማት ውስጥ ፈጠራ እና ዘላቂነት"/Innovations and Sustainability in Modern Tourism Development"/" በሚል መሪ ሀሳብ በርካታ የምርምር ሥራዎችና ቁልፍ መልዕክት ቀርቧል።
የምርምር ኮንፈረንሱ ቁልፍ መልዕክት አቅራቢ የሆኑት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም እንደ ገለጹት ዘላቂነትን ማረጋገጥ ቱሪዝምን ከአካባቢ ጥበቃ እና ከማህበረሰብ ተጠቃሚነት ጋር
በማጣመር ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ውጤት ማስመዝገብ እና ፈጠራን ማስፋፋት እንደሆነ ገልጸዋል።
በሌላም በኩል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና የከተማ ዲዛይኖችን በመጠቀም የጎብኝት ልምድ ማሳደግ እና ሀገራዊ ገጽታን መገንባት ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።
ፈጠራ እና ቱሪዝም በኢትዮጵያ የማይነጣጠሉ በመሆኑ አዳዲስ በቴክኖሎጂ የታገዘ የቅርሶች ገለጻ (AR/VR) ፣ ቀልጣፋ የዲጂታል ክፍያ እና የቦታ ማስያዣ (Reservation) የመሳሰሉ ዘዴዎችን መጠቀም ዋናዎች ናቸው ብለዋል።
በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት ፈጠራ ፣ ዘላቂነት እና ዘመናዊነት አቀናጅቶ መሰራት እንዳለበት በመልዕክቱ ተገልጿል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official