‘ንቁ የዲጂታል ብልህነት ለሥራ ፈጠራ’ በሚል ርዕስ ለተቋሙ ሠራተኞችና ሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ቱ.ማ.ኢ
ግንቦት 7/2018 ዓ.ም
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከሸጋ ትውልድ ማህበር ጋር በመተባበር በተቋሙ ለሚገኙ ሠራተኞች፣ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች ንቁ የዲጂታል ብልህነት ለሥራ ፈጠራ በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ አምስት ሚለዮን ኮደሮች በማስመዝገብና በማሰልጠን ለዜጎች ሥራ ዕድል እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በዚህ ፕሮግራም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት በኢትዮጵያ መንግስት ተነሳሽነት ዓለም አቀፍ በሆኑ አራት ስልጠና አይነት ስልጠናዎችን ሁሉም ዜጋ እንዲሰለጥን ተመቻችቷል፡፡ስለሆነም የተቋሙ ሠራተኞችና ሰልጣኞች በዚህ የኢትዮጵያ አምስት ሚለዮን ኮደሮች ስልጠና ውስጥ እንዲያልፉ በሸጋ ትውልድ አስተባባሪነት ሁሉም ከምዝገባ እስከ ምስክር ወረቀት አወሳሰድ ያለው ግንዛቤ አግኝቶ ወደ ስልጠና እንዲገቡ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
የተቋሙ አመራር እና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው ሠራተኞች ይህን ስልጠና በመውሰድ ተጨማሪ የሥራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስልጠና መሆን እንደለበት ተናግረው ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ በዚሁ ልክ የሚራመድ ሰራተኛ፣አሰልጣኝ እና ሰልጣኝ እንደተቋም ለመፍጠር በፍጥነት የዚህ ስልጠና ተጠቃሚ ኢንዲሆኑ እድሉ እንደተመቻቸ ገልጿል።
የሸጋ ትውልድ ባለራዕይና መስራች አቶ ሳሙኤል ገረመው በዚህ ፕሮግራም ሦስት ነገሮች ለማድረግ እንደመጡ ጠቁመው እነሱም ለማስተማር ለማጽናትና ለማብቃት ነው በማለት ከምዝገባ እስከ ምስክር ወረቀት አወሳሰድ ያለውን በከፍተኛ የኮምፒውተር ባለሙያዎች ስልጠናው እንደሚሰጥ ገልጸዋል። በስልጠናው ወቅት የሸጋ ትውልድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተው ስልጠናውን በተግባር አሰልጥነዋል። በስልጠናውም የተቋሙ ሰራተኞች፣አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በመሳተፍ ከዚህ በፊት በራሳቸው ተነሳሽነት ስልጠናውን ከወሰዱት ውጪ ያሉት ሁሉም እንዲመዘገቡና ስልጠናውን እንዲጀምሩ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less