ኢንስቲትዩቱ በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ በዲግሪ እና በደረጃ 350 ሰልጣኞች ለ58ኛ ጊዜ አስመረቀ። ሐምሌ 11/2018 ዓ ም

July 20, 2026
ኢንስቲትዩቱ በቱሪዝምና በሆቴል ዘርፍ  በዲግሪ እና በደረጃ   350 ሰልጣኞች ለ58ኛ ጊዜ አስመረቀ። ሐምሌ 11/2018 ዓ ም

የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለ58ኛ ጊዜ በቱሪዝም እና በሆቴል ዘርፍ በዲግሪ እና በደረጃ ያስለጠናችውን ሰልጣኞች በድምቀት አስመርቋል ።
በምርቃው መርሃ ግብር የተገኙት የኢንስቲትዩቱ የቦርድ ሰብሳቢ እና የክብር እንግዳ የክብር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ተመራቂዎች አሁን ሀገራችን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታና እያደገ ከመጣው የቱሪስት መዳረሻዎች ልማት አንጻር፣ የተማሩትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የሀገርን ገጽታ በመገንባትና የኢኮኖሚውን ዘርፍ በማነቃቃት ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።
በምርቃው መርሃ ግብር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታችው ነጋሽ ተቋሙ ሀገሪቱ በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ የምትፈልገውን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሰው ኃይል ለማፍራት ያለውን ራዕይና ተልዕኮ በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላይ በርካታ አዳዲስና ግዙፍ የቱሪስት መስህቦችን (የኮሪደር ልማቶችንና የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችን ጨምሮ) እያስመረቀች ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ እነዚህ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ወደ ሥራ መሰማራታቸው የዘርፉን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻልና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ያለው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ነው መሆኑንም ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ይህንን ፕሮግራም ላዘጋጁት አካላትም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በትምርታችው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሰልጣኞች የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት ተሰጥቷል፤ በተጨማሪም የትብብር ስልጠና አብሮን ለሚሰሩ ሆቴሎችና የቱሪዝም ድርጅቶች የምስጋና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል፡፡ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less