የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን ገመገመ።

August 05, 2026
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት  አፈፃፀሙን ገመገመ።

ቱ ማ ኢ ሐምሌ 25/2018 ዓ ም የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መድረክ በተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ባሉን የሥራ ክንውኖች እና የተገኙ ውጤቶች የሠራተኞችና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ መንግስት የሰጠውን ትኩረት እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ከመሠረተ ልማት ግንባታ ጎን ለጎን የሚሄድ የሰው ኃይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ይገባናል ብለዋል።
የተቋሙ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና አጠቃላይ ተቋማዊ እንቅስቃሴዎችን ገልጸዋል።
በዕለቱ ፕሮግራም የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ በአቶ ዳግም አዲሱ የቀረበ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች ተዳስዋል።
የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ፡ የዕቅድና በጀት፣ ክትትልና ግምገማ ከፍተኛ ባለሙያ በአቶ ሽመልስ ማሰረሻ ለተሳታፊዎች ቀርቦ መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኗል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less