"የዛሬ ህፃናት የነገ ተስፋ ናቸው።''
ኢንስቲትዩቱ በሆሳዕና ከተማ የመዋዕለ ህፃናት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አኖረ
ቱማኢ
ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በጀሎ ናረሞ ቀበሌ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን የመዋዕለ ህፃናት ግንባታ መሠረት ድንጋይ የማኖር እና ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ ተውልድን የመገንባት ሥራውን እያስቀጠለ መሆኑን እና የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መሠረት ለሆኑ ህፃናት ዘመናዊ የመዋዕለ ህፃናት መገንባቱ በህፃናት አዕምሯዊ ዕድገት ላይ ሊኖር የሚችለውን ጉልህ ሚና አስረድተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በገለፃቸው ኢንስቲትዩቱ ደረጃውን የጠበቀ የመዋዕለ ህፃናት መገንባት ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት ቁሳቁስ እንደሚሟላም አሳውቀዋል።
'' የዛሬ ህፃናት የነገ ተስፋ ናቸው።''በሚል የተቀመጠው የማዋዕለ ህፃናት ግንባታ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲውል አስፈላጊው ክትትል እደሚያደርጉ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከግንባታው ባሻገር ለአንድ ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ለሆሳዕና ከተማ ከንቲባ ለአቶ ሳሙኤል ሽጉጤ እና ለትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊው አስረክበዋል።
ክቡር ከንቲባው በከተማው የመዋዕለ ህፃናት ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ በመቀመጡ እና በክረምት የበጎ ተግባር አገልግሎት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለማከናወን እዚህ በመምጣታችሁ የኢንስቲትዩቱን አመራርና ሠራተኞች ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል ። የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችም መርቀዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less