የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በሀምበሪቾ ኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ ስፍራ ጉብኝት አደረጉ።

August 05, 2026
የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በሀምበሪቾ  ኢኮ ቱሪዝም  መዳረሻ ስፍራ ጉብኝት አደረጉ።

የቱሪስት መዳረሻዎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሰው ሀይል ልማት ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው:- የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት
(ሆሳዕና ፣ሀምሌ 26/2018 ዓ.ም) የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለሞያዎች በሀበሪቾ ኢኮ-ቱሪዝም ስፍራ ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ በጉብኝቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሀበሪቾ ኢኮ-ቱሪዝም ስፍራ ማራኪ መልክዓ-ምድራዊ ገፅታ ያለዉ ተራራ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢንስቲትዩት ከ50 ዓመት በላይ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ሲደግፍ የነበረ አንጋፋ ተቋም ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በደረጃ አራትና በዲግሪ ደረጃ ሰልጣኞችን በማሰልጠን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ስራ ዕድል የሚያዘጋጅ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት በስልጠና ፣በማማከር ፣በማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በባህላዊ ምግብና መጠጥ ልማት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ በክልሉ የሚገኙ ባህላዊ ምግቦችን እና መጠጦችን በማጥናት ለትውልድ እንዲተላለፍ እንዲሁም የምግብ ሜኖ ሆነው እንዲወጡ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በአዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረው ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በማቅረብ ቱሪስቶች እንዲቆዩና ለሀገር ተጨማሪ ገቢ እንዲያስገኙ ተደርጓል።
በኢትዮጵያ በርካታ የቱሪዝም ስፍራዎች ቢኖሩም የመጎብኘት ልምድ አናሳ በመሆኑ የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ማስፋፋት ይገባል ብለዋል።
እንደዚ አይነት ጉዞዎች ህብረብሔራዊ ኢትዮጵያን እውን በማድረግ የህዝብ ለህዝብ ትስስር በማጠናከር ብሄራዊ ትርክት ለማስረፅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
ተቋሙ ለረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪውን የሰው ሀይል ፍላጎት ለሟሟላት ለዜጎች ሙያዊ ስልጠና በመስጠት እንዲሁም የጥናትና ምርምር በማድረግ አገልግሎቱ እንዲሻሻል እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የተቋሙን ሠራተኞች በማህበራዊ አገልግሎት በማሳተፍ አብሮት እና ወዳጅነት በማጠናከር በሀገር ግንባታ ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም አስታውቀው በትናትናው ዕለት በሆሳዕና ከተማ የመዋዕለ ህፃናት ግንባታ መሠረት ድንጋይ መጣላቸውን አስታውሰዋል።
የከምባታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተክሌ ስዩም እንደተናገሩት በአካባቢው በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ይህንን መሸከም የሚችል የቱሪስት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የዞኑን የቱሪዝም መዳረሻዎ የማልማት ስራ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ ተጨማሪ ሁለት 777 ደረጃዎች በመገንባት የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከፍ ማድረግ ተችሏልም ብለዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሀምበሪቾን የኢትዮጵያዊያን መንደር ለማድረግ ያስቀመጡት የመሠረት ድንጋይ ሎጆችን ጨምሮ በርካታ የቱሪስት አገልግሎቶችን የያዘ በመሆኑ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።
ሀምበሪቾ ተራራ ከምባታ ቀድሞ የሰፈረበትና የህዝቡ ታሪክ የተጠነሰሰበት፣ ባህላዊ አስተዳደር ስርዓት ማሳያ መሆኑንም ገልፀው ተራራው በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም መዳረሻነትን ዕውቅና አግኝቶ በጋራ የማልማት ሥራዎችም ተጀምሯል ብለዋል።
በኤልያስ ቲርካሶ
ከሴንትራል ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን See less