ጥሩ የደንበኛ አገልግሎት ለተቋም ስኬት ፤
ለደንበኞች እርካታ፣ ለተቋሙ መልካም ገጽታ እና ለተቋማዊ ውጤታማነት ያለውን ወሳኝ ሚና የሚያጠናክር መነሻ የጥናት ጽሑፍ ቀረበ፡፡
ቱ ማ ኢ
ነሐሴ 5/2018 ዓ ም
የፌዴራል ቱሪዝም ማስልጠኛ ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ክፍል በየሁለት ሳምንቱ በተለያዩ የሙያዊና የተቋም ጉዳዮች ላይ የመነሻ የጥናት ጽሑፍ እያቀረበ ውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፤ በዚህ መርሃ ግብርም “Good Customer Service as a Driving Force for TTI's Institutional Success” በሚል ርዕስ በቀረበ ሰነድ መነሻነት ውይይት ተካሄዷል።
የውይይቱን መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የቱሪዝም ማስልጠኛ ኢንስቲትዩት አሰልጣኝ ጌታሁን ደሳለኝ ሲሆኑ፣ ጥሩ የደንበኛ አገልግሎት ለተቋም ስኬት፣ ለደንበኞች እርካታ፣ ለተቋሙ መልካም ገጽታ እና ለተቋማዊ ውጤታማነት ያለውን ወሳኝ ሚና ያጠነክራል ያሉትን ሃሳብ በዝርዝር አቅርበዋል።
የውይይቱ ዋና ዓላማ በኢንስትኢትዩቱ የሚሰጠውን የደንበኛ አገልግሎት በማሻሻል የተማሪዎች፣ ሠራተኞች፣ የኢንዱስትሪ አጋሮችና ባለድርሻ አካላት እርካታን ማሳደግ እና ለተቋሙ ዘላቂ ስኬት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ማጠናከር ነው ብለዋል።
የጥናትና ምርምር ክፍሉም እንዲህ ያሉ ቀጣይነት ያላቸው የዕውቀት ሽግግር መድረኮችን በማጠናከር የኢንስቲትዩቱን ተቋማዊ አፈጻጸም ጥራት ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
በውይይቱ አሰልጣኞች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/tticommunication
ቴሌግራም ፡https://t.me/tticommunication
http://tiktok.com/@ftti_official See less