ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሐምሌ 6/2014 ዓ.ም”ተቋሙን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ ከሁላችን የሚጠበቅ ውጤት አለ” አቶ ጌታቸው ነጋሽ
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እና የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች አቶ ሀብታሙ ክብረት፣ አቶ ገዛኸኝ አባተ እና አቶ ይታሰብ ስዩም ከሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በመግቢያቸው እዚህ የተመደብነው አዳዲስ እና ነባር አመራሮች ከእናንተ ጋር በመሆን ለዘርፉ መንግስት የሰጠውን ትኩረት መሰረት ያደረገ ተቋሙን ከፍ ወዳለ ደረጃ ማሳደግ የሚጠበቅብን ውጤት አለ ብለዋል፡፡ ተቋማችን በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲው ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ሆኖ መቀጠል እንዲችል በትኩረት መሥራት ይጠበቅብናል በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
የተቋሙ ነባር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ሪፖርት እና የ2015 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም ከመምህራን እና ከሰራተኞች የቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ሁሉም አመራሮች ከተነሱ ነጥቦች አኳያ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል፡፡
ተቋሙ ላለፉት 10 ዓመታት ከኢንስቲትዩት ወደ ማዕከል በመውረዱ ምክንያት የእድሜውን ያህል ለዘርፉ ማበርከት ያለበትን የሰለጠነ የሰው ሃይል ማቅረብ እንዳይችል ተግዳሮት እንደነበረበት በተለያዩ አጋጣሚዎች ማንሳታችን የሚታወስ ሲሆን በዚህ ዓመት ወደ ኢንስቲትዩት አድጎ ቀድሞ ከነበረው አቅም በተሻለ አመራር ከሀገራችን አልፎ ከምስራቅ አፍሪካ ካሉ አቻ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችለውን የበጀትና የሰው ሃይል ድጋፍ ማድረጉ በእጅጉ የሚያበረታታ ነው፡፡
Recent Comments